ፕሮግራሙን ከጤና ኤክስቴንሽን ጋር በማስተሳሰር የዘመነ የክትባት ክፍል መፍጠር ይገባል

ፕሮግራሙን ከጤና ኤክስቴንሽን ጋር በማስተሳሰር የዘመነ የክትባት ክፍል መፍጠር ይገባል፦ ገስጥ ጥላሁን

‎‎ሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ከህፃናት አድን ድርጅት ጋር በመሆን በክትባት አገልግሎት ዙሪያ የተሟጋች ቡድን ዉይይት አካሄደ።

‎‎ሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ እና ህፃናት አድን ድርጅት በጋራ በመሆን ከሀይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች ፣ ከአጋር ሴክተር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ከሚመለከታቸዉ ባለሞያዎች ጋር በመሆን ህፃናት አድን ድርጅት በሚሰራባቸዉ ዋድላ እና አንጎት ወረዳዎች የክትባት አፈፃፀም እንዲሻሻል የተሟጋች ቡድን ዉይይት አካሂደዋል።

‎‎በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሐላፊ አቶ ገስጥ ጥላሁን ፕሮግራሙን ከጤና ኤክስቴንሽን ጋር በማስተሳሰር የዘመነ የክትባት ክፍል እና የተሻሻለ የክትባት ግብአት አያያዝ ስርዓት መፍጠር ይገባል ብለዋል።

‎‎ሃላፊው አያይዘውም ፕሮግራሙ የክትባት አገልግሎቱን ከሌሎች የጤና ስራዎች ጋር በማስተሳሰር አቅምን አሟጦ በሀብትም በሀሳብም መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

‎‎የጤና ትምህርት እና ተግባቦት ስራዉ ተሳፊዎችን እና ታላሚዎችን መሰረት በማድረግ የጤና ንቃተ ህሊና ያደገ ማህበረሰብ መፍጠር ይገባል ያሉት አቶ ገስጥ የምንፈልገዉን የጤና ስርአት ለመፍጠር በተግባቦት ስራ ላይ መስራት ይገባል ብለዋል።

‎የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ ሲ/ር ፈለቁ መኮነን በበኩላቸው ሁለቱ ወረዳዎች በተለየ መልኩ በዚህ ፕሮጀክት እየተደገፉ የልህቀት ማዕከል በመሆን የሌሎች ወረዳዎች የልምድ መቀመሪያ ሆነዉ ማገልገል አለባቸዉ ሲሉ ገልጸዋል።

‎

‎ወረዳዎቹ በፕሮጀክቱ ካልታቀፉ ወረዳዎች በተሻለ መፈፀም አለባቸዉ ያሉት ሲ/ር ፈለቁ በተለይ ለክትባት ቤተሰቦች አመች የሆነ ማህበረሰቡ የሚገለገሉበት የክትባት ክፍል እና ጤና ተቋም መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል።

Get 30% off your first purchase

X