የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የሱፐርቪዥን ቡድን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ሜዴክስ ኢትዮጵያ የስራ እቅስቃሴ ተመልክተዋል

‎ሜዴክስ ኢትዮጵያ ለክልሉ ማህበረሰብ የመድሀኒት አቅርቦት አገልግሎት እየሰጠ ነው።

‎

‎በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲ/ር ክሽን ወልዴ የተመራ የድጋፍ ቡድን በጤና ተቋማት ያገኙትን ግብረ መልሶችና የተነሱ ጥያቄዎችን ሜዴክስ እንዴት መፍታት ይችላል እየተሰራ ያለውን ስራስ እንዴት ማጎልበት ይችላል የሚል ጥያቄዎችን በማንሳት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ጠቁመዋል።

‎በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲስተር ክሽን ወልዴ ተቋሙን ተዘዋውረው በተመለከቱበት ወቅት እንደተናገሩት አሁን ላይ ለክልሉ ጤና ተቋማት እና ህዝብ ችግር የሆነውን መሰረታዊ መድሃኒት በማቅረብ ሂደት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል።

‎የሜዴክስ ኢትዮጵያ ስራ-አስኪያጅ ዶክተር ብዙአየሁ ጋሻው በበኩላቸው ድርጅቱ በክልሉ ከተቋቋመ 7 ዓመት በላይ ያስቆጠረ ነው ብለዋል።

‎ዶክተር ብዙአየሁ ጋሻው አክለውም ሜዴክስ በክልሉ ደሴና ባህር ዳር በሁለት ቅርንጫ ለማህበረሰቡና ለጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም በቂ ባለመሆኑ በቀጣይ በጎንደር ከተማ ሶስተኛ ቅርንጫፍ ለመክፈት ማቀዱን ተናግረዋል።

‎የጤና ስርዓቱ ችግሮች በማኒፋክቸሪግ፣ የአገልግሎት ተደራሽ መሆን፣ ጥራትን ማስጠበቅ እና ህብረተሰቡ ላይ ያለውን የወጭ ጫና መቀነስ ሜዴክስ በዋናነት አላማ አድርጎ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ብዙአየሁ ጋሻው ናቸው።

‎በቀጣይም በክልሉ ውስጥ ያሉ ጤና ተቋማት ሜዴክስ ጋር ያላቸው የግብይት መጠን እንዲያድግ ህግና አሰራሩን ተከትለው መስራት እንደሚያስፈልግ ስራ አስኪያጁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎

‎ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም

Get 30% off your first purchase

X