የጤና ኢኒሼቲቮችን በልዩ ቅንጅትና ቁርጠኝነት መምራት ይገባል

፦ አበበ ተምትሜ ‎ ‎የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የድጋፍ ቡድን አባላት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ በመገኘት የአካል ድጋፍ አደረጉ። ‎ ‎ድጋፍ እና ክትትሉ በበጀት ዓመቱ በጎንደር ክላስተር በሚገኙ ልዩ ልዩ የጤና ተቋማት የተመዘገቡ ውጤቶችን እና የታዩ ጉድለቶችን በመለየት የክልሉን ህዝብ በጤናው ዘርፍ ፍትሃዊ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ ‎ ‎የድጋፍ ቡድኑ በበጀት ዓመቱ በዞኑ እየተከናወኑ የሚገኙ የጤና ልማት ስራዎች አፈጻጸሞችን መገምገምና የቀጣይ ወራት ተግባራትን መደገፍ ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል። ‎ ‎የድጋፍ ቡድኑን የመሩት በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አበበ ተምትሜ ዞኑ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን መልካም ተግባራት አድንቀው በቀሪ ወራት በትኩረት ሊሰሩ የሚገባቸውን ተግባራት ጠቁመዋል። ‎ ‎መምሪያው በዋናነት ካለፈው ዓመት ትምህርት በመውሰድ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ላይ በትኩረት በመስራት ውጤት ማስመዝገብ እንዳለበት አንስተው የድጋፍ ቡድኑ ዓላማም ይህንኑ ለመደገፍ መሆኑን ገልጸዋል። ‎ ‎ኢኒሼቲቮችን በልዩ ቅንጅነትና ቁርጠኝነት መምራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ሃላፊው ሁሉንተናዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ መሰረታዊ የጤና አገልግሎትን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። ‎ አመራሩና ባለሙያው የጤና ዕቅዱን ለማሳካት ሙሉ ጊዜውን በስራው ላይ ማዋል አለበት ያሉት አቶ አበበ አገልግሎት ፈላጊውን ማህበረሰብ ማርካት የሚቻለው ባለሙያው በሚሰጠው ቀልጣፋ አገልግሎት መሆኑን ተናግረዋል። ‎ ‎በውይይት መድረኩ በዝቅተኛ ደረጃ የተፈፀሙ ተግባራትን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል። ‎ ‎የድጋፍ ቡድኑ በጎንደር ክላስተር ( ጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን፣ ሰሜን ጎንደርና እና ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን) ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ በመገኘት ድጋፉን ጀምሯል። ‎ ‎ድጋፍ እና ክትትሉ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት የጤና መምሪያው ጨምሮ እስከ ወረዳ ድረስ በመውረድ በሆስፒታሎች እና በጤና ጣቢያዎች ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

Get 30% off your first purchase

X