ሜዴክስ ኢትዮጵያ ለክልሉ ማህበረሰብ የመድሀኒት አቅርቦት አገልግሎት እየሰጠ ነው።
በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲ/ር ክሽን ወልዴ የተመራ የድጋፍ ቡድን በጤና ተቋማት ያገኙትን ግብረ መልሶችና የተነሱ ጥያቄዎችን ሜዴክስ እንዴት መፍታት ይችላል እየተሰራ ያለውን ስራስ እንዴት ማጎልበት ይችላል የሚል ጥያቄዎችን በማንሳት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ጠቁመዋል።
በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲስተር ክሽን ወልዴ ተቋሙን ተዘዋውረው በተመለከቱበት ወቅት እንደተናገሩት አሁን ላይ ለክልሉ ጤና ተቋማት እና ህዝብ ችግር የሆነውን መሰረታዊ መድሃኒት በማቅረብ ሂደት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የሜዴክስ ኢትዮጵያ ስራ-አስኪያጅ ዶክተር ብዙአየሁ ጋሻው በበኩላቸው ድርጅቱ በክልሉ ከተቋቋመ 7 ዓመት በላይ ያስቆጠረ ነው ብለዋል።
ዶክተር ብዙአየሁ ጋሻው አክለውም ሜዴክስ በክልሉ ደሴና ባህር ዳር በሁለት ቅርንጫ ለማህበረሰቡና ለጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም በቂ ባለመሆኑ በቀጣይ በጎንደር ከተማ ሶስተኛ ቅርንጫፍ ለመክፈት ማቀዱን ተናግረዋል።
የጤና ስርዓቱ ችግሮች በማኒፋክቸሪግ፣ የአገልግሎት ተደራሽ መሆን፣ ጥራትን ማስጠበቅ እና ህብረተሰቡ ላይ ያለውን የወጭ ጫና መቀነስ ሜዴክስ በዋናነት አላማ አድርጎ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ብዙአየሁ ጋሻው ናቸው።
በቀጣይም በክልሉ ውስጥ ያሉ ጤና ተቋማት ሜዴክስ ጋር ያላቸው የግብይት መጠን እንዲያድግ ህግና አሰራሩን ተከትለው መስራት እንደሚያስፈልግ ስራ አስኪያጁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም