በጠለምት ወረዳ ደጃች ሜዳ ጤና ጣቢያ የእናቶች የቀዶ ህክምና አገልግሎት ተጀመረ

ሆስፒታሎች በቅርበት በሌሉበት ወረዳ እና ከተሞች ላይ የእናቶች ቀዶ ሕክምና መስጫ ማዕከላትን ለማስፋፋት እየሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።

‎‎የቢሮው ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አበበ ተምትሜ ‎እናቶች የሁሉም ነገር መሠረት መሆናቸውን ገልጸው የጤናው መስክ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው አንዱ እና ዋናው የእናቶች እና ህጻናትን ሞት መቀነስ መሆኑን አመላክተዋል።

‎‎ሃላፊው አያይዘውም የቀዶ ሕክምና አገልግሎት መጀመሩ በተለይ በወሊድ ወቅት ቀዶ ህክምና ሲያስፈልጋቸው በሪፈር ወደ ደባርቅ እና አዲ አርቃይ የሚደረገውን ጉዞ ያስቀራል ያሉ ሲሆን ለሞት እና እንግልት እንዳይዳረጉ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል።

‎‎የአገልግሎቱ መጀመር የጤና ጣቢያውን አገልግሎት ተጠቃሚ ቁጥር ይጨምራል ያሉት አቶ አበበ ጤና ጣቢያው መድሃኒቶችን ጨምሮ ግብዓቶችን ማሟላት እንዳለበት ጠቅሰዋል።

‎‎የተጀመረውን አገልግሎት ማስቀጠል እንደሚገባም አቶ አበበ አሳስበዋል።

‎‎የጤና ጣቢያው ባለሙያዎችም በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆነው ለማህበረሰቡ እየሰጡት ላለው አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበዋል

የሰሜን ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ ልዑል ብርሐኑ በበኩላቸው ያለው ሀብት ውስን በመሆኑ በአግባቡ መጠቀም ይገባል ያሉ ሲሆን ማህበረሰቡ ከጤና ጣቢያው ጎን ሆኖ መደገፍ አለበት ብለዋል።

‎ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የእናቶችና ህጻናት ሞት ለመቀነስ መምሪያው ከአጋር ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የክልል፣የዞንና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የምክር ቤት አባላት እና የአካባቢዎች ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

Get 30% off your first purchase

X