በውይይቱ የቢሮው የድጋፍ ቡድን አባላት፣የሆስፒታሉ የቦርድ ተወካዮች፣አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የአዲስ ዓለም ሆስፒታል ጽዱ፣ማራኪ፣ለሰራተኛውና ለተገልጋዩ ምቹ በማድረግ በተሰሩ ስራዎች መደነቃቸውን የገለጹት ሲ/ር ክሽን ወልዴ ለለውጡ ለተጉ የሆስፒታሉ የቦርድ አመራሮች፣የማኔጅመንት አባላትና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።
ሆስፒታሉ በእናቶችና ህጻናት ጤና በተመላላሽና ተኝቶ ህክምና እየሰጠ ያለው የጤና አገልግሎት መሻሻሉን ገልጸዋል።
የህብረተሰቡን እርካታ ያረጋገጠ የጤና አገልግሎት ለመስጠት አመራሩና ባለሙያው እንዲተጋ አሳስበዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ሆስፒታሉ ያሉበትን የክፍል ጥበት ለመፍታት ተጨማሪ የማስፋፊያ ግንባታ ህንጻ ገንብቶ ማጠናቀቁን ተናግረዋል።
ሆስፒታሉ ያሉበትን የሰው ሀይል ፣የግብዓት፣የመድሀኒትና የህክምና መሳሪያ እጥረት ለመፍታት ቢሮው አቅም በፈቀደ መጠን ለመፍታት ጥረት ያደርጋል ብለዋል።
የውስጥ ገቢ አቅምን በማሳደግ የራስን ችግር በራስ ለመፍታት የአካባቢውን ማህበረሰብና ባለሀብቶች በማስተባበር ጥረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል ።
የባለሙያዎች ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ለመፍታት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ቢሮው ላካሄደው ድጋፋዊ ጉብኝት ተሳታፊዎች አመስግነዋል።